ሐምሌ 16 ቀን 2013

ከአሰብነው እንደርሳለን

ድሉ ጉዞን ለጀመሩ ሰዎች ሳይሆን ጉዞን ለጨረሱ ሰዎች ነው። እና እኛ ኢትዮጵያውያን ሁሌም የጀመርነውን በመጨረስ እንጅ የጀመርነውን በማቋረጥ አንታወቅም በተሠለፍንበት መንገድ አሸናፊነታችንን ለማብሰር ጊዜ አይፈጅብንም ።
የአባይ ግድብን ስንጀምር ብዙዎች አይችሉትም አያደርጉትም ብለው ተሳልቀውብን ነበር ። በአሽሙርም በጎንም እያጨበጨቡ በዛኛው ጎን ይሸረድዱን ነበር።
ጉዟችንን ስንቀጥል ግብፅ መደናገጡንና መደናበሩን ጀመረችና እርዳታና ብድር ለማስከልከል ያልወጣችው ያልወረደችው ያልፈነቀለችው የተንኮል አይነት አልነበረም። ግን ምን ዋጋ አለው ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ ነው እና የሀገሬው ተረት ጉዟችንን አንድ በመሆን ቀጠልን። በጉዞ ውስጥ እንቅፋት ሁሌም አይጠፋም ዋናው ግን እንቅፋቱን በማለፋ ያሠቡበት ግብ መድረስ ነው።
የቆመ ሰው እግሩን እንቅፋት አይመታውም፤ በፍጥነት በተጓዝክ ቁጥር በእንቅፋት የመመታት እድልህ ይጨምራል ቢሆንም ግን የሆነ ቦታ መድረስህ አይቀርም ፡፡ አዎ አጀማመርህ እንደፈለከው ላያምር ፤ ዋናው ነገር ግን ዋጋ መክፈል ያለብህ አጨራረስህን ለማሳመር ነው!
ይህን ማድረግ ደግሞ ዛሬ ሳይሆን ትናንት ከትናንት ወዲያ በአድዋ በካራማራ የጀግንነት አልበገር ባይነታችንን አስመስክረናል ፡፡ ያንን ነው ዛሬም በአባይ ላይ እያደረግን ያለነው ።
ይህ ለኛ ኢትዮጵያውያን ብርቃችን አደለም እኛ ማለት እኮ የዓለም ሚዛን ፣ የጥበብ ምንጭ ፣ የስልጣኔ መጀመሪያ የሠው ልጅ መገኛ ነን፡፡ ወደቁ ሲሉን የምትንነሳ የምንበረታ ፣ ሁልጊዜም አሸናፊ የሆነን ነን፤ ኢትየጵያ ደግሞ አሸናፊዎችን የወለደች ሀገር ናት – ኢትዮጵያ፡፡
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን በረጅም ዘመን ታሪካቸው አያሌ ችግሮች ገጥመዋቸው ሁሉንም በጥበብ አልፈው ሌላ ዘመን ላይ ደርሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ ችግሮች ውስጣዊ ብቻ አይደሉም፤ የውጭም ናቸው እንጂ፤ ኢትዮጵያን ለመዋጥ የሚቋምጡና በኢትዮጵያ ረዘም ባለ ታሪክ የሚበሳጩ ጠላቶቿ በየዘመናቱ በውስጧ ችግር በታዬ ቁጥር በጎን ያሰፈስፋሉ፡፡
ዳሩ የውጭውም የውስጡም ጠላት ያስበዋል እንጂ ሳይሳካለት ተያይዞ ያልፋል፤ ኢትዮጵያዊነትን የሚችል የለምና፡፡
ሁለተኛውን ሙሌት እንዳንሞላ ብዙ ተፅኖ ለመፍጠር ቢሞከርም እኛ ግን ለተወረወረ ድንጋይ መልስ ሳንሰጥ ግድባችን ገንብተን ሙሌታችን በድል አጠናቀናል ተደብቀን ሳይሆን ለጠላቶቻችን በሚገባቸው ቋንቋ ደብዳቤ ተይበን አሳውቀናቸዋል። ዓለምም ጭምር እንዲያውቅ አድርገናል ፡፡
ማንም ደግሞ በኛ ፍላጎት ላይ ምንም ሊጭንብን አንደማይችል በተግባር አሳይተናል። በዚህም አንድነታችን ጎልቶ ወቷል ሰራዊታችን ጁንታውን በገባበት ገብቶ ድባቅ እየመታ ታሪክ አስመዝግቧል። ከውጭ ለሚመጣ ጠላትም ሁሌ ዝግጁ መሆኑ እንዲያውቁት አድርጓል።
ህዝብ ነው ሀያል ክንዳችን -ሰላም ልማት ነው ቋንቋችን
የመፈቃቀር አንድነት -እኩልነት ነው ዜማችን
በማለት ግልፅ አድርጎ አስቀምጧል አሁንም ሆነ ነገም ህዝባዊ አንድነታችን በማጠናከር በአገኘነው ድል ሳንኩራራ ጠንክረን መስራትና መበርታት ይገባናል።
በአሁኑ ሰዓትም መርጠናል፤ ተክለናል፤ ሞልተናል ይህ ስኬታችንን እናስቀጥለዋለን።ያሰብነውን ከማሳካት ማንም የሚያግደን የለም በሠራዊታችን እና በህዝባችን አንድነት ጁንታውን ከስሩ በመንቀል ልማታችንን እናስቀጥላለን። ግድባችንን በመገደብ እና በማጠናቀቅ ለህዝባችን የረጅም ጊዜ የመልማት ፋላጎት ከግብ እናደርሳለን።
ድሉ ጉዞን ለጀመሩ ሰዎች ሳይሆን ጉዞን ለጨረሱ ሰዎች ነው።
 
Source : FDRE Facebook
ሻምበል ሰለሞን ጫኔ